በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካርቱም የአየር ድብደባው ዛሬም ቀጥሏል


ካርቱም፣ ሱዳን
ካርቱም፣ ሱዳን

የአንድ ሳምንት ተኩስ አቁም ዛሬ ምሽት እንደሚጀምር ይጠበቃል

የሱዳን ሠራዊት ዛሬ በመዲናዋ ካርቱም የአየር ድብደባ ማድረጉን ነዋሪዎች ተናገረዋል። ይህም ከትናንት በስቲያ ቅዳሜ ከተደረሰውና፣ በሱዳን ሰዓት አቆጣጠር ዛሬ ከምሽቱ ለአስር ሩብ ጉዳይ ከሚጀምረው ተኩስ ማቆም በፊት የበላይነትን ለማግኘት ነው ተብሏል።

የሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች፣ ማለትም፣ የጦር ሠራዊቱ ዋና አዛዥ የጀኔራል አብደል ፋታህ አል ቡርሃን እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዥ ሞሃመድ አምዳን ዳጋሎ ወኪሎች፣ በአሜሪካ እና በሳዑዲ አረቢያ አደራዳሪነት፣ ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ለአንድ ሳምንት ተኩስ እንድሚያቆሙ ቅዳሜ ዕለት ጀዳ ውስጥ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ስምምነቱ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስና መሠረታዊ አገልግሎቶች መልሰው እንዲጀምሩ ያስችላል የሚል ተስፋ አሳድሯል።

ሠራዊቱ ትናንት ዕሁድ ማምሻውንም የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ተሽከርካሪዎችን ኢላማ ያደረገ የአየር ድብደባ እንዳደረገ የአይን ምሥክሮችን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ግጭቱ ሚያዚያ 7 ከጀመረ አንስቶ የፈጦኖ ደራሽ ኃይሉ ወታደሮች በመዲናዋ ካርቱም የመኖሪያ አካባቢዎችን መሠረት በማድረግ እንደሚንቀሳቀሱ ታውቋል።

ውጊያው 1.1 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ሲያፈናቅል፣ 250 ሺሕ የሚሆኑትን ደግሞ ወደ ጎረቤት አገራት እንዲሸሹ አድርጓል። ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑት ህይወታችውን እንዳጡ ይገመታል። ዛሬ ተደርጓል የተባለው የአየር ድብደባ በመዲናዋ ካርቱም፣ ኦምዱርማን እና ባህሪ ከተሞች እንደተፈጸም የየከተሞቹ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG