በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል ቡርሃን ዲፕሎማሲያዊ ጥረታቸውን በመቀጠል ወደ ቱርክ አቅንተዋል


የሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል አብዱልፋታህ አል ሲሲ
የሱዳን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል አብዱልፋታህ አል ሲሲ

በሱዳን ዳርፉ ዛሬ በተፈጸመ የአየር ድብደባ 40 የሚሆኑ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ በሚነገርበት ወቅት፣ የሀገሪቱ ጦር አዛዥ ወደ ቱርክ ማቅናታቸው ታውቋል።

የሱዳኑ ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጀኔራል አብዱልፋታህ አል ሲሲ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ 5ኛ የሆነውን የውጪ ጉብኝት በማድረግ፣ ከቱርኩ ፕሬዚንት ሬቸፕ ታይፕ ኤርዶዋን ጋራ ለመነጋገር አንካራ ገብተዋል።

“የሁለትዮሽ ግንኙታቸውን በተመለከተ እና ያንንም በሚያጠናክሩበት መንገድ ላይ ይነጋገራሉ” ሲል የአል ቡርሃን ቢሮ አስታውቋል።

ባለፈው ሚያዚያ በእርሳቸው ታማኝ ኃይል እና ቀድሞ ምክትላቸው እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አዛዥ ጀኒራል ሞሃመድ ሃምዳን ዳግሎ መካከል ግጭት ከጀመረ አንስቶ፣ እስካለፈው የፈረንጆች ወር መጨረሻ ድረስ ቡርሃን በካርቱም በሚገኝ ወታደራዊ ሰፈር ተወስነው የሰነበቱ ሲሆን፣ አሁን ግን በቀይ ባሕር ባህር ዳርቻ የምትገኘውን የፖርት ሱዳን ከተማ ማዘዣ ጣቢያቸው አድርገዋል።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ ቡርሃን ወደ ግብጽ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኳታር፣ እና ኤርትራ ተጉዘው ከሀገራቱ መሪዎች ጋር ተነጋግረዋል። ድርድር የሚደረግ ከሆነ ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ የሚያደርጉት ጥረት እንደሆነ ተንታኞች በመናገር ላይ ናቸው።

እስከአሁን የ7ሺህ 500 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል የተባለው ግጭት ዛሬ ረቡዕ፣ በተለይም በዳርፉር ጋብ አላለም።

በደቡብ ዳርፉር መዲና በሆነችው ኒያላ በተፈጸመ የአየር ድብደባ 40 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

ድብደባው በሁለት ገበያዎች እና በከተማው መንደሮች ላይ እንደተፈጸመ፣ የሕክምና ባለሙያዎች እና የዐይን እማኞች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG