በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ዑመር ዐል ባሽር ፍ/ቤት ቀረቡ


የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ዑመር ዐል ባሽር
የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ዑመር ዐል ባሽር

የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ዑመር ዐል ባሽር የተመሰረተባቸው የሙስና ክስ ሂድት እንዲጀመር ዛሬ በካርቱም ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ለሰላስ ዓመታት ያህል ሥልጣን ላይ ከቆዩ በኋላ ባለፈው ሚያዝያ ወር ከሥልጣን የተወገዱት ባሽር ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ የውጭ ምንዛሬ ተገኝቶባቸዋል። ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ሥጦታዎችን ተቀብለዋል የሚል ክስ ነው የተመሰረተባቸው።

አንድ መርማሪ ፖሊስ በፍርድ ቤቱ ቃላቸውን በሰጡት መሰረት ከሳውዲ አረብያ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮች መቀበላቸውን ባሽር ለመርማሪዎች ተናግረዋል።

75 ዓመት ዕድሜ የሆናቸው ባሽር ነጭ ባህላዊ ልብስ ለብሰው በፍርድ ቤቱ ከታጠረ የእስረኛ ክፍል ላይ ሆነው የፍርዱን ሂደት ሲከታተሉ እንደነበር ተዘግቧል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በበኩሉ የሙስና ክሱ በቀድሞው ፕሬዚዳንት ላይ የተመሰረተውን ከባድ ክስ ሊያድበሰብስ አይገባም ይላል።

በሱዳን ዳርፉር ክልል ለረጅም ጊዜ ሲካሄድ ከቆየው ጦርነት ጋር በተይያዘ ዓለም ቀፍ የወንጀል ችሎት ባሽርን የጦርነት ወንጀልና ፍጅት ፈፅመዋል የሚል ክስ የመሰረተባቸው መሆኑ የሚታወቅ ነው።

ባለፈው ግንቦት ወር ደግሞ አገዛዛቸውን የተቃወሙ ሰዎችን በመግደል ተግባር ተሳትፈዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG