በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሱዳን ሠራዊት ወደ ማዕከላዊ ካርቱም እየተቃረበ መሆኑን አስታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ በሱዳን ጦር እና በወታደራዊ ሃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በከተማው የሚታይ ጭስ፣ ካርቱም እአአ መስከረም 2024
ፎቶ ፋይል፦ በሱዳን ጦር እና በወታደራዊ ሃይሎች መካከል በተፈጠረ ግጭት በከተማው የሚታይ ጭስ፣ ካርቱም እአአ መስከረም 2024

የሱዳን ሠራዊት ከተለያዩ አቅጣጫዎች በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ቁጥጥር ሥር ባለውና "ሪፐብሊካን ፓለስ" የተሰኘው ፕሬዝደንታዊ መኖሪያ በሚገኝበት ማዕከላዊ ካርቱም ላይ ጥቃቱን አጠናክሯል።

ከሚያዚያ 2015 ዓ/ም ጀምሮ ከፈጥኖ ደራሽ ኅይሉ ጋራ በመፋለም ላይ ያለው የሱዳን ሠራዊት መዲናዋን ካርቱም መልሶ ለመቆጣጠር ባለፉት ሣምንታት ውስጥ ከበድ ያለ ጥቃት ሲሰነዝር ቆይቷል።

ሠራዊቱ ከ"ሪፐብሊካን ፓለስ" ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

“ኃይሎቻችን ማዕከላዊ ካርቱም ሊደርሱ ተቃርበዋል። የዳግሎ ሚሊሺያንም እያስወጣ ነው” ሲሉ አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የሠራዊቱ ምንጭ ለኤ.ኤፍ.ፒ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

አል ረሚላ የተሰኘውን እንዲኹም በማዕከላዊ ካርቱም የኢንዱስትሪ መንደሮችን መቆጣጠሩን ሠራዊቱ ትላንት ረቡዕ አስታውቋል።

የዐይን እማኞች እንደሚሉት ግን ሠራዊቱ ወደፊት ለመገስገስ በረጃጅም ሕንጻዎች የሚገኙትን የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ አልሞ ተኳሾችን ሾልከው ማለፍ አለባችው።

የኤኤፍፒ ዜና አገልግሎት የፈጥኖ ደራሽ ኅይሉን አስተያየት ለማካተት ሞክሮ መልስ ማግኘት አለመቻሉን አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG