በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዓለም አቀፍ ለጋሾች ለሱዳን 2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገቡ


በሱዳን የተፈጠረውን ግጭት ሸሽተው የተሰደዱ የመጠጥ ውሃ ለመቅዳት ጀሪካን ይዘው ወረፋ እየተጠባበቁ በምሥራቃዊ ቻድ
በሱዳን የተፈጠረውን ግጭት ሸሽተው የተሰደዱ የመጠጥ ውሃ ለመቅዳት ጀሪካን ይዘው ወረፋ እየተጠባበቁ በምሥራቃዊ ቻድ

ዓለም አቀፍ ለጋሾች ለሱዳን የ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

ትናንት ፓሪስ ላይ በተካሄደው የሱዳን ሰብአዊ ረድኤት ዓለም አቀፍ ጉባዔ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ ለሱዳን ተጨማሪ 100 ሚሊዮን ዶላር እንደምትለግስ ቃል ገብታለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዊሊያም ሽመንሲስ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል በሱዳን ያለው ሰብአዊ ሰቆቃ በአሁኑ ወቅት በዓለም ከሁሉም አስከፊው መሆኑን ገልጸዋል። በሁለቱ ጀነራሎች የሥልጣን ትግል ሳቢያ የተቀሰቀሰ ጦርነት አንድ ዓመት እንዳስቆጠረ ጠቅሰው በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸውን፣ ስምንት መቶ ሺህ ሰዎች መፈናቀላቸውን እና 25 ሚሊዮን ሰዎች ሰብአዊ ርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አውስተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ፓሪሱ ጉባዔ ላይ ይፋ ያደረገችው ተጨማሪ ድጋፍ አስቸኳይ የምግብ ርዳታ እንዲሁም የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት እና ሌላም ወሳኝ የሆኑ ርዳታዎችን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህ ተጨማሪ ርዳታ ጋራ ዩናይትድ ስቴትስ ለሱዳን የለገሰችው አጠቃላይ ርዳታ አንድ ቢሊዮን ዶላር መድረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባዩ አክለው አመልክተዋል።

ርዳታው የህክምና እና የንጽህና አገልግሎቶች ሌሎችም ሰብዊ ድጋፎችንለማቅረብ እንዲሁም በጦርነቱ ምክንያት ተፈናቅለው በአጎራባች አገሮች የተጠለሉ ስደተኞችን ለመርዳት እንደሚውል አስረድተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG