በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሱዳን ውስጥ በተካሄደ ግጭት ሰባት ሰዎች ተገደሉ


ሱዳን ውስጥ ባለፈው ሳምንት መጫረሻ ላይ በተካሄደው ግጭት ሰባት ሰዎች ተገድለዋል ሲሉ የሀገሪቱ የአገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስትር ዛሬ ለምክር ቤት ተናግረዋል።

ስድስቱ ሰዎች የተገደሉት ካርቱም ላይ ፕረዚዳንት ኦማር ዐል-ባሽር ከሥልጣን እንዲወርዱ ሲጠይቁ የነበሩ የተቃውሚ ሰልፈኞችን ለመበተን የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ እንደሆነ ሚኒስትሩ ገልፀዋል። አንድ ሰው ደግሞ ዳርፉር ውስጥ በተመሳሳይ ተቃውሞ መገደሉን ሚኒስትሩ ቡሽራ ጁማ ተናግረዋል።

ጁማ በገለጹት መሰረት 10,000 የሚሆኑ የተቃውሞ ስለፈኞች ባለፈው ቅዳሜ በወታደራዊው ዋና ጽህፈት አካባቢ መሰለፋቸውን፣ ጠቁመዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG