በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ዋድ አልኑራ መንደር ቢያንስ 104 ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ


ሱዳን ዋድ አል ኑራ መንደር
ሱዳን ዋድ አል ኑራ መንደር

በሱዳን ዋድ አል ኑራ መንደር የፈጥኖ ደራሽ ድጋፍ ሃይሎች በመባል የሚታወቁት ኅይሎች ባደረሱት ጥቃት በአንድ ቀን በትንሹ 104 ሰዎች ተገድለዋል ሲል የሱዳን ለዲሞክራሲ ተሟጋቾች ኮሚቴ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አመለከተ።

ካላፈው ዓመት ሚያዝያ ጀምሮ ከመደበኛው ጦር ሠራዊት ጋር ውጊያ ላይ የሚገኘው ፈጥኖ ደራሹ ጦር ከባድ መሣሪያዎችን በመጠቀም መንደሩን በሁለት አቅጣጫዎች በማጥቃት መጠነ ሰፊ ጉዳት እና መፈናቀል ሳያደርስ እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

ኮሚቴው በማህበራዊ ድህረ-ገጾች ባሰራጨው ምስል ከመንደሩ አደባባይ የተገኘ የጅምላ መቃብር ሲል የገለጸውን አሳይቷል።

በሱዳን በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል፣ በአንዳንድ መረጃዎች እስከ 150,000 ይደርሳሉ ሲል ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

“የፈጥኖ ደራሹ ጦር በሱዳን የተለያዩ አካባቢዎች መንደሮችን በማጥቃት፣ በመዝረፍ እና ጾታዊ እና የጎሳ ጥቃቶችን በመፈጸም የታወቀ ነው” ሲል የኮሚቴውን መግለጫ የጠቀሰው ዘገባ አመልክቷል፡፡ የሱዳን ገዥ ሉዓላዊ ምክር ቤት ጥቃቱን “መከላከያ በሌላቸው ሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈፀመ አሰቃቂ እልቂት” ሲል አውግዞታል፡፡

የሱዳን ጦር ሠራዊትና የፈጥኖ ደራሹ ጦር ሲቪሎችን ኢላማ በማድረግ እና ሰብዓዊ እርዳታን ማደናቀፍን ጨምሮ በጦር ወንጀሎች እንደሚከሰሱ ዘገባው አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG