በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትናንቱ የሞቃድሾ ፍንዳታ አራት ሰዎች ተገደሉ


የሶማሊያ መንግሥት ቃል አቀባይ ሞሃመድ ኢብራሂም ሞአሊሙ ላይ የመቁሰል አደጋ ማድረሱ ይታወሳል፣ እአአ ጥር 16/2022
የሶማሊያ መንግሥት ቃል አቀባይ ሞሃመድ ኢብራሂም ሞአሊሙ ላይ የመቁሰል አደጋ ማድረሱ ይታወሳል፣ እአአ ጥር 16/2022

በሶማሊያ መዲና ሞቃድሾ፣ በዋዳጅር ወረዳ ትናንት በተካሄደ የአጥፍቶ መጥፋት የቦምብ ጥቃት፣ አራት ሰዎች ሲገደሉ፣ 10 ደግሞ መቁሰላቸው ተገለጠ፡፡

የሶማሊያ ፖሊስ እንዳስታወቀው፣ ተቀጣጣይ ፈንጅዎቹን ታጥቆ ወደ አንድ ሻይቤት የገባው አጥፍቶ ጠፊ፣ ሻይ ሊጠጣ እንደገባ ደንበኛ ገብቶ ከተቀመጠ በኋላ፣ በራሱ ላይ የተመጠደውን ፈንጅ ማፈንዳቱ ተመልክቷል፡፡

በሌላ በኩልም ይህ ጥቃት ከተፈጸመ ሁለት ሰዓት በኋላ፣ እዚያው ወረዳ ውስጥ በመኪና ላይ ተጠምዶ የነበረ የቦምብ ፍንዳታ ቢደርስም፣ በዚህኛው ጥቃት የደረሰ ጉዳት አለመኖሩ ተነገሯል፡፡

አልሸባብ ወዲያውኑ ለጥቃቶቹ ኃላፊነቱን መውሰዱን አስታውቋል፡፡

ባላፈው እሁድ በደረሰ ተመሳሳይ ጥቃት የሶማሊያ መንግሥት ቃል አቀባይ ሞሃመድ ኢብራሂም ሞአሊሙ ላይ የመቁሰል አደጋ ማድረሱ ይታወሳል፡፡

ሞአሊሙ ለከፍተኛ ህክምና ወደ ቱርክ መላካቸው ተገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG