በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍጋኒስታን ካቡል በአጥፍቶ ጠፊ ቦምብ አምስት ሰዎች ተገደሉ


ዛሬ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ በካቡል አንድ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ታጣቂ ጥቃት አድርሶ በትንሹ አምስት ሰዎችን ሲገድል ሌሎች ዘጠኝ አቁስሏል።

ዛሬ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ በካቡል አንድ አጥፍቶ ጠፊ ቦምብ ታጣቂ ጥቃት አድርሶ በትንሹ አምስት ሰዎችን ሲገድል ሌሎች ዘጠኝ አቁስሏል።

በከተማዋ ከሚገኝ አንድ ባንክ ውጪ ጥቃቱ የደረሰው የአፍጋኒስታን ጦር ሠራዊት አባላትና የሌሎች የደኅንነት ተቋማት ሠራትኞች ወርሃዊ ደሞዛቸውን ለመቀበል ተራ ይዘው እየጠበቁ ባለበት ወቅት መሆኑን የዓይን ምስክሮች ተናግረዋል።

ታሊባን ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።

ይህ የዛሬው ከባድ ጥቃት የተፈጸመው አፍጋኒስታን የኢድ-አልፈጢርን በዓል ለማክበር እየተዘጋጀች ባለችበት ወቅት መሆኑም ታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ ድሮኖች ሌሊቱን ባደረሱት ጥቃት ሕጻናትና ሴቶችን ጨምሮ 13 ሲቪሎችን መግደላቸውንና ሌሎች ሠባት ማቁሰላቸውን የሂራት ክልላዊ መንግሥት ቃል አቀባይ ጄላኒ ፋርሃድ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG