ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት 110 ፍልሰተኞችን አሳፍረው የነበሩ ሁለት ጀልባዎች ቱኒዥያ ጠረፍ ላይ ተገልብጠው ሴቶችና እና ሕፃናትን ጨምሮ 27 ሰዎች ሞቱ፡፡
ኤኤፍፒ ባለሥልጣናት ጠቅሶ እንደዘገበው ሁለቱ ጀልባዎች የተገለበጡት በማዕከላዊ ቱኒዝያ በከርከናህ ደሴቶች አቅራቢያ ነው፡፡
የነፍስ አድን ሠራተኞች 83 ሰዎችን ያዳኑ ሲሆን 15ቱ ሆስፒታል ገብተዋል፡፡ ደብዛቸው የጠፉ ሌሎች ተሳፋሪዎችን የማፈላለግ ሥራ ቀጥሏል።
ቱኒዚያ እና ሊቢያ መደበኛ ያልሆነ ስደት ዋና መነሻዎች ናቸው፡፡ የጣሊያኗ ደሴት ላምፔዱዛ 150 ኪሎ ሜትር ብቻ ይርቃል ስደተኞቹ ወደ አውሮፓ ለመድረስ አስበው ነበር።
ቱኒዚያውያንን ጨምሮ በየዓመቱ ከኢኮኖሚ ችግር የሚሰደዱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደገኛውን የሜዲትራኒያን መሻገር ይሞክራሉ።
መድረክ / ፎረም