በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስለኮቪድ ክትባት አዲስ ጥናት


በፋይዘር እና ባዮንቴክ እና በባዮንቴክ የመድሃኒት ኩባኒያዎች የተቀመመው የኮቪድ-19 ክትባት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የተከሰተውን የኮሮናቫይረስ ዝርያ ለመቋቋም የሚያስችለው የተፈጥሮ መከላከያ በመጠኑ ዝቅተኛም ቢሆን ቫይረሱን እንደሚከላከል አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ።

የፋይዘር እና የቴክሳስ ዩኒቨርስቲ የህክምና ክፍል ተመራማሪዎች ዛሬ በኒው ኢንግላንድ መጽሄት ላይ ሪፖርታቸውን አውጥተዋል። የደቡብ አፍሪካውን አዲስ ዓይነት ቫይረስ ተመሳሳዩን ፈጥረው የፋይዘሩን ክትባት ሁለቱንም ዙር ከተወጉ ሰዎች ላይ የተወሰደ የደም ናሙና ምን ያህል እንደሚከላከለው ሲያጠኑ፣ ባገኙት ውጤት መሰረት ክትባቱ በመጀመሪያው ቫይረስ ላይ ካለው የመከላከል ዓቅም ጋር ሲነጻጸር ተቀይሮ ብቅ ባለው ዝርያ ላይ ያለው የመከላከል ዓቅም በሁለት ሦስተኛ ዝቅ ያለ ሆኖ አግኝቶታል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ሞደርና ኩባኒያ በበኩሉ በኒውንግላንድ የህክምና መጽሄት ላይ ባወጣው ሪፖርት በሁለት ዙር በሚሰጠው የኮቪድ-19 ክትባት ላይ ከፋይዘሩ ክትባት ጋር ተመሳሳይ ውጤት እንዳገኘ አመልክቷል።

ፋይዘር እና ባዮንቴክ ክትባታቸውን አሻሽለው ለመቀመም ወይ ደግም በመጀመሪያ የሚሰጠውን ክትባት ዓቅም የሚያጠናክር ተጨመሪ ክትባት ለማሰናዳት፣ ከመድሃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣናት ጋር እየተነጋገሩበት መሆኑን አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG