በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ተቋም እንደ አዲስ እንዲደራጅ ተጠየቀ


የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ተቋም እንደ አዲስ እንዲደራጅ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:49 0:00

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ተቋም እንደ አዲስ እንዲደራጅ ተጠየቀ

የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ ተቋም እና በሥሩ ያለው መዋቅር የገለልተኝነት ችግር ያለበት እና ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት የተጫነው መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ። መልካም አስተዳደር በአፍሪካ በተባለ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት የተደገፈውን ጥናት የሠሩት የሕግ ባለሞያ እና አማካሪ አቶ ደበበ ኀይለ ገብርኤል የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ገለልተኝነቱን በማጣቱ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የተለያዩ ችግሮች እንደሚስተዋሉ ለቪኦኤ በሰጡት አስተያየት ገልጸዋል፡፡

አሁን የሚታዩት ችግሮች እንዲቀረፉ ተቋሙ እንደ አዲስ እንዲደራጅና ተጠሪነቱም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆንን አቶ ደበበ በጥናታቸው አመልክተዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አንድ የዘርፉ ባለሞያ ደግሞ ሲቪል ሰርቪሱ ከፍተኛ የገለልተኝነት ችግር እንዳለበት የተገለጸውን አጠናክረው ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲሆን በሚል በቀረበው ምክረ ሐሳብ ላይ ግን እንደማይስማሙ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG