በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩናይትድ ስቴትስ ተማሪዎች የሀገሪቱ ም/ቤት መሳርያ ቁጥጥር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ

ተማሪዎች በዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊትና በምክር ቤት ህንፃ ፊት የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄዱ
ተማሪዎች በዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊትና በምክር ቤት ህንፃ ፊት የተቃውሞ ሰልፍ እያካሄዱ

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች የሀገሪቱ ምክር ቤት መሳርያ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ውሳኔ አለመውሰዱን በመቃወምና በአንድ የፍሎሪዳ ትምህርት ቤት ላይ የተገደሉትን ተማሪዎች ለማሰብ ከትምህርት ቤቶቻቸው ወጥተዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች የሀገሪቱ ምክር ቤት መሳርያ ላይ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችል ውሳኔ አለመውሰዱን በመቃወምና በአንድ የፍሎሪዳ ትምህርት ቤት ላይ የተገደሉትን ተማሪዎች ለማሰብ ከትምህርት ቤቶቻቸው ወጥተዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ተማሪዎች የሀገሪቱ ም/ቤት መሳርያ ቁጥጥር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:55 0:00

የተማሪዎቹ ተቃውሞ ለ17 ደቂቃዎች ያህል የዘለቀ ሲሆን በፍሎሪዳ የተገደሉትን 14 ተማሪዎችንና 3 ጎልማሶችን ለእያንዳንዳቸው ለአንድ ደቂቃ ያህል አስበዋቸዋል። አንድ የ19 ዓመት ዕድሜ ወጣት ከአንድ ወር በፊት ማርጀሪ ስቶንማን ዳግለስ በተባለው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተኩስ ከፍቶ እንደፈጃቸው የሚታወስ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መምርያ ምክር ቤት የውሁዳኑ መሪ ናንሲ ፔሎሲ ዋሺንግተን በተካሄደው ተቃውሞ ንግግር ሲያደርጉ አስቸኳይ መፍትሄ የሚጠይቀውን እምነታችሁን ወደ ምክር ቤቶቹ ህንፃ ደጃፍ በማድረሳችሁ እናማስግናለን” ብለዋል።

ተቃውሞውን ያስተባበሩት ሰዎች እንደሚሉት በሀገሪቱ ዙርያ ወደ ሦሥት ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቶቻቸው እንዲወጡ ታቅዷል። በዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥት ፊት ለፊትና በምክር ቤት ህንፃ ፊት የተቃውሞ ሰልፍ እንዲካሄድ ነው የታቀደው። ሌሎች ደግሞ ካለፈቃድ የወጡት ተማሪዎች ይቀጣሉ ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG