በኢትዮጵያ፣ ቋሚ ወርኃዊ ደመወዝ ያላቸውና ዝቅተኛ ተከፋይ ነዋሪዎች፣ በየጊዜው የሚጨምረውን የዋጋ ንረት መቋቋም እየከበዳቸው እንደ መጣ፣ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
በዐዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር ሰውአለ አባተ፣ የብር የመግዛት ዐቅም በየጊዜው እየተዳከመ መምጣት፣ ቋሚ ወርኃዊ ደመወዝተኞችን በኑሮ ውድነቱ እንዲጎዱ አድርጓቸዋል፤ ይላሉ፡፡ በዚኹ ታሳቢነት መንግሥትም፣ የደመወዝ ጭማሬ ሊያደርግ እንደሚገባ፣ ዶክተር ሰውአለ ይመክራሉ፡፡
መንግሥት በበኩሉ፣ ለሠራተኛው የሚደረግን የደመወዝ ጭማሬ፣ ወደፊት የሚያየው ጉዳይ እንደኾነ፣ ከዚህ በፊት አስታዉቋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም