በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዘንድሮው የጎልደን ግሎብስ ሽልማት


የሰማንያኛው ጎልደን ግሎብ የምርጥ ድሬክተር ሽልማት አሸናፊው ዕውቁ አሜሪካዊ ፊልም ሠሪ ስቲቨን ስፒልበርግ
የሰማንያኛው ጎልደን ግሎብ የምርጥ ድሬክተር ሽልማት አሸናፊው ዕውቁ አሜሪካዊ ፊልም ሠሪ ስቲቨን ስፒልበርግ

በአጠቃላይ በተንቀሳቃሽ ሲኒማ እና "ዘ ፊብልማንስ" በተባለው ፊልሙ የሰማንያኛው ጎልደን ግሎብ የምርጥ ድሬክተር ሽልማት አሸናፊው ዕውቁ አሜሪካዊ ፊልም ሠሪ ስቲቨን ስፒልበርግ በትናንትናው ምሽት በካሊፎርኒያ ግዛቷ የቢቨርሊ ሂልስ ከተማ በተካሄደው ሥነ ስርዓት ለሽልማት ከበቁት የዘንድሮው ተሸላሚዎች መካከል አንዱ ነው።

እንደ “ጃውስ” .. “ሽንድለርስ ሊስት” እና “ሴቪንግ ፕራይቬት ራያን” የተባሉትን የመሰሉ ድንበር ተሻጋሪ የሲኒማ ሥራዎቹ የ76 አመት ባለ ጸጋው የፊልም ድሬክተር ስፒልበርግ ይህ ሦስተኛው የጎልደን ግሎብስ ሽልማቱ ነው። ከዚህ ቀደም “ሽንድለርስ ሊስት” እና “ሴቪንግ ፕራይቬት ራያን” በተሰኙት ፊልሞቹም ለተመሳሳይ ሽልማት በቅቶ ነበር።

****

ስለ ሁለት ጠበኛ የአየርላንድ ተወላጆች ጨለምተኛ ታሪክ የሚተርከው “ዘ ባኒሽስ ኦፍ ኢኒሽሪን” በሙዚቃዊ ድራማው ዘርፍ አሸናፊ ሲሆን፤ የፊልም ሰሪው ማርቲን ማክዶናግም ለምርጥ ተውኔት የተዘጋጀውን፣ ኮሊን ፋረል ደግሞ በኮሜዲ ሲኒማ ዘርፍ የኮከብ ተዋናይ ሽልማቶችን ተቀዳጅተዋል።

በሲኒማዊ ድራማ ዘርፍ "ኤልቪስ” በተሰኘው ፊልም የሮክ ኤንድ ሮል ሙዚቃውን ንጉስ ሆኖ በመጫወት ላሳየው ልዩ ክህሎት ኦስቲን በትለር የምርጥ ተዋናይ ሽልማት ባለቤት ሲሆን፣ "ታር" በተሰኘው ፊልም የአእምሮ መታወክ የገጠማትን የሲምፈኒ ሙዚቃ መሪ ሆና የተጫወተችው ኬት ብላንሼት ደግሞ ለኮከብ ሴት ተዋናይ የተሰናዳውን ሽልማት ተቀብላለች።

****

ከታዳሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ባተረፈ “ብላክ ፓንተር፣ ዋካንዳ ፎርኤቨር” በተሰኘው ፊልም ላይ ባሳየችው ድንቅ የአጨዋወት ብቃት የረዳት ተዋናይ የሽልማት ዘርፍ የምርጥ ተዋናይ ሽልማት በመቀበል የማርቨል ስቱዲዮ የሰራውን የኩምክና ለዛ የተላበሰ ፊልም ለጎልደን ግሎብስ ሽልማት በማብቃት የመጀመሪያዋ ተዋናይ በመሆን ታሪክ ሰርታለች።

ከሑይ ኳን “ኤቭሪቲንግ ኤቭሪዌር አት ዋንስ” በተሰኘው ፊልም በተባባሪ ተዋናይነት የተጫወተው የምርጥ ተዋናይነት ሽልማት ሲጎናጸፍ ሚሼል ዮህ ደግሞ በሙዚቃዊ ድራማ የሽልማት ዘርፍ ላሳየችው ብቃት ያለው አጨዋወት አሸናፊ ሆናለች።

ሽልማቹን የሚሰጠው አካዳሚ አዋርድስ በደነገገው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የቴሌቭዥን ትዕይንቶችን እና የተለያዩ ፕሮግራሞችን ጨምሮ ለምርጥ ሥራዎች ልዩ ሽልማት የሚያጎናጽፈው የጎልደን ግሎብስ ሽልማት የሆሊውድ የሽልማቶች መድረክ የአመቱ ከፋች ሥነ ስርአት ነው።

ሆኖም ዋናው እናት ድርጅት የሆሊውድ የውጭ ፕሬስ ማህበር አንድም በኃላፊነት የሥራ መደብ ያለ ጥቁር ጋዜጠኛ እንደሌለው ከታወቀ እና ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ስነ ምግባር ነክ ችግሮች አንዳሉት ከተገለጸ በኋላ የኤንቢሲ የቴሌቭዥን ጣቢያ ባለፈው ዓመት ሥነ ስርአቱን መሉ በሙሉ ሰርዞት አንደነበር ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG