በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስቲቭ ጆብስ


독일 프랑크푸르트의 애플스토어에 놓여진 사진과 꽃
독일 프랑크푸르트의 애플스토어에 놓여진 사진과 꽃

ስቲቭ ጆብስ ሞተ፤ ታላቅ ሥራውን ግን ለሰው ልጆች አበረከተ፡፡ ስቲቭ ዓለምን የለወጠ፣ ባለ ብሩህ አዕምሮና ጀግና ሆኖ አለፈ፡፡

የአፕል ኮምፕዩተር ኩባንያ ተባባሪ መሥራች ስቲቭ ጀብስ ያረፈው ባደረበት የጣፊያ ካንሰር በ56 ዓመት ዕድሜው መስከረም 24 ቀን 2004 ዓ.ም ነበር፡፡

ዛሬ ድፍን ዓለም ኀዘኑን እየገለፀ ውሏል፡፡ ይህንን ታላቅ ሰው እያከበረው፣ እየዘከረው ይገኛል፡፡

የጆብስ ፈጠራዎች የዓለም ኢንዱስትሪዎችን አሠራርና የሰው ልጅን የዕለት ከዕለት ሕይወትና ኑሮ፣ የጉዞውንም መንገድ፣ ፍጥነትና አቅጣጫ ለውጠዋል፡፡

አቶ ተሻገር ተስፋዬ በካሊፎርኒያው የሣይበር ሣይንስና ቴክኖሎጂ ቀበሌ በሲሊኮን ቫሊ የሚገኝ ኤሌክትሪካል ኢንጂነር፣ ቴክኖሎጂስትና ኢንቬስተር ነው፡፡ ስለ ስቲቭ ጆብስ ሕይወትና ማንነት ለአሜሪካ ድምፅ አድማጮች ዕውቀቱንና ሃሣቡን አካፍሏል፡፡

ውይይቱን ያዳምጡ፡፡

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG