በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተኩስ አቁም መታወጁ ትክክለኛ እርምጃ ነው - የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር


ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት
ፎቶ ፋይል፦ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት

“የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ሰኔ 21/2021 ዓ.ም. የወሰደው ‘በሰብዓዊ ምክንያት ተኩስ የማቆም አዋጅ’ ትግራይ ውስጥ ላለውን ግጭት መፍትኄ ለማግኘት ትክክለኛ እርምጃ በመሆኑ እንደግፈዋለን” ሲሉ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ዛሬ ባወጡት መልዕክት አስታውቀዋል።

ትግራይ ውስጥ ዘላቂ ሰላም እንዲገኝ መንገድ ለመጥረግ እንዲቻልም የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት አጠቃላይና ሁሉን አቀፍ የሆነ ቋሚ ተኩስ ማቆም ላይ እንዲደረስ እንዲሠሩ የኅብረቱ ሊቀ መንበር ጠይቀዋል።

ለዚህም ሁሉም ዓይነት የፀብ ሁኔታዎች እንዲቆሙ፤ በዓለምአቀፍ ህግ መሠረት ሲቪሎችን ከአደጋ ለመጠበቅና ክልሉ ውስጥ ለተጎዱት ሁሉ እጅግ አስፈላጊ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ የሰብዓዊ እርዳታ ተዋናዮች ደኅንነቱ የተረጋገጠ ተደራሽነት እንዲኖራቸው ለማስቻል ሁሉም ወገኖች ኃላፊነቶቻቸውን እንዲወጡ ሊቀ መንበር ማህማት ጥሪ አድርገዋል።

ለትግራይ ግጭት የፖለቲካ መፍትኄ እንዲፈለግም ሊቀ መንበሩ በተጨማሪ መጠየቃቸውንና በሃገሪቱ ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ሁሉንም ኢትዮጵያዊ ጥረቶች የአፍሪካ ኅብረት ድጋፉን ለመስጠት ያለውን ያልተቋረጠ ዝግጁነት ማሳወቃቸውን ከፅህፈት ቤታቸው የወጣው መግለጫ ይጠቁማል።

XS
SM
MD
LG