በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌዴራል ፖሊስ ስለ እሥራቶችና ፍተሻዎች ተናገረ


የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ ብሔር ተኮር እስራቶች እየተካሄዱ መሆኑን የሚናገሩ ዘገባዎች “እውነት አይደሉም” ሲል የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስተባብሏል።

የኮሚሽኑ የኮምዩኒኬሽንስ ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ በተለይ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ምርመራዎችንና ተከናውነዋል ያሏቸውን ተግባራት አብራርተዋል።

በዐዋጁ መሠረት በተደረገው ምርመራ በርከት ያለ ቁጥር ያላቸው ሰዎችና ህገወጥ የጦር መሣሪያዎች፤ እንዲሁም “የጥፋት ተግባርን ያግዛሉ” ያሏቸው ቁሳቁሶች በቁጥጥር መዋላቸውን ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀኃፊ የጅምላ ፍጅት ጉዳዮች ልዩ አማካሪ ዋሪሙ ንዴሪቱ ከትናንት በስተያ ባወጡት መግለጫ የድርጅታቸው ሠራተኛ የሆኑ ሰዎችን ጨምሮ የትግራይ ተወላጆች እየታሠሩ ናቸው ሲሉ አድራጎቱን በጥብቅ እንደሚያወግዙ አስታውቀው ነበር።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ፌዴራል ፖሊስ ስለ እሥራቶችና ፍተሻዎች ተናገረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:47 0:00


XS
SM
MD
LG