በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ እና ሩስያ ስለሰሜንኮሪያ

ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን እና የሩስያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ የኮሪያ ባህረ ገብ አካባቢ ከኒውክሊየር ነፃ እንዲሆን የሚያስችል የዲፕሎማሲ መፍትኄ ላይ እንዲደረስ መሥራታቸውን ሊቀጥሉ መስማማታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን እና የሩስያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ የኮሪያ ባህረ ገብ አካባቢ ከኒውክሊየር ነፃ እንዲሆን የሚያስችል የዲፕሎማሲ መፍትኄ ላይ እንዲደረስ መሥራታቸውን ሊቀጥሉ መስማማታቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ስቴትስ ዲፓርትመንት ዛሬ ባወጣው መግለጫ መሰረት ትናንት ማክሰኞ በስልክ የተወያዩት ሁለቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የሰሜን ኮሪያ የኒውክሊየር መርኃ ግብር የሰላም ጠንቅነት እና ያቺ ሃገር የባለኒውክሊየር መሣሪያ ኃይል እንድትሆን ዩናይትድ ስቴትስም ሆነች ሩስያ እንደማይቀበሉ ተነጋግረዋል።

የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባወጣው መግለጫ በበኩሉ የዋሺንግተን የወራሪነት አነጋገር ኮሪያ ባህረ ገብ ላይ ውጥረቱን ያባባሰው መሆኑን ሚስተር ላቭሮቭ ለዩናይትድ ስቴትሱ አቻቸው ሬክስ ቲለርሰን አስታውቀዋቸዋል፡፡ ያ ደግሞ በሩስያ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌለው ነግረዋቸዋል ብሏል።

ይህ በዚህ እንዳለ የዩናይትድ ስቴትስ የገንዘብ ሚኒስቴር በሁለት የሰሜን ኮሪያ ባለልሥጣናት ላይ በሀገሪቱ የተወንጫፊ ሚሳይል ግንባታ መርኃ ግብር በተጫወቱት ሚና የተነሳ ማዕቀብ ጥሎባቸዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ርምጃውን የወሰደችው የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታ ምክር ቤት ሰሜን ኮሪያ የምታስገባውን ነዳጅ መጠን የሚገድብ ውሳኔ በሙሉ ድምፅ ማፅደቁን ተከትሎ ነው።

ከሰሜን ኮሪያ በሚወጡም ሆነ በሚገቡ እና የተከለከሉ ጭነቶችን ይዘዋል ተብለው የሚጠረጠሩ መርከቦች ላይ ፍተሻው እንዲጠብቅ የፀጥታ ምክር ቤቱ ውሳኔ ፈቅዷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG