በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሮሒንግያ ሙስሊሞችን ከባንግላዴሽ ወደ ማያንማር የመመለሱ ሂደት


የሮሒንግያ ሙስሊሞች
የሮሒንግያ ሙስሊሞች

የሮሒንግያ ሙስሊሞችን ከባንግላዴሽ ወደ ማያንማር የመመለሱ ሂደት መዘግየቱ ተነገረ።

የሮሒንግያ ሙስሊሞችን ከባንግላዴሽ ወደ ማያንማር የመመለሱ ሂደት መዘግየቱ ተነገረ።

የመመለሱ ፕሮግራም ነገ ማክሰኞ እንደሚጀመር ተገልፆ የነበረ ቢሆንም፣ መቼ በውል እንደሚጀምር የተሰጠ መግለጫ የለም።

ማያንማርና ጎረቤቷ ባንግላዴሽ በቅርቡ በደረሱት የጋራ ሥምምነት፣ ወታደራዊ ጥቃትና ግድያ ሽሽት ወደ ባንግላዴሽ የኮበለሉት የሮሒንግያ ሙስሊሞች በቅርቡ ወደ ማያንማር እንደሚመለሱ ነበር የተወሰነው።

አብዱል ካላም የባንግላዴሽ የስደተኞች ርዳታና ማቋቋሚያ ኰሚሽነር እንዳሉት “ዋናው ቁምነገር፣ ስደተኞቹ የሚመለሱት በገዛ ፈቃዳቸው መሆኑ ነው” ሲሉ፣ ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል።

ስደተኞቹ ከቅርብ ወራት ወዲህ ጥለውት ወደመጡበት ቦታ ያለ ፈቃዳቸው እንዳይመለሱ፣ የረድዔት ሠራተኞችና ሮሒንግያኖች ሥጋት አላቸው።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG