በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በስሪላንካ አመጹ ተባብሶ ቀጥሏል


ስሪላንካ ውስጥ የተከሰተው ህዝባዊ አመፅ
ስሪላንካ ውስጥ የተከሰተው ህዝባዊ አመፅ

የኢኮኖሚና የፖለቲካ ቀውሱን ተከትሎ ስሪላንካ ውስጥ የተከሰተው ህዝባዊ አመፅ በተቆጡ ተቃዋሚዎችና በፀጥታ ኃይሎች መካከል ወደተፈጠረ አመፅና ሁከት አዘል ግጭት ተባብሶ መቀጠሉ ተዘግቧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ራኒል ዊክሬሜሲኒግሄ በመላ ሃገሪቱ ላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጣሉ ሲሆን ተቃዋሚዎቹ ዋና ከተማዪቱ ኮሎምቦ ላይ ቢሯቸውን በመውረር ሰብረው ለመግባት ሙከራ ማድረጋቸው ተሰምቷል።

ሁከቱ የተፈጠረው ሥልጣናቸውን ላለመልቀቅ ሲሟገቱ የቆዩት ፕሬዚዳንት ጎታባያ ራጃፓክሳና ባለቤታቸው አገር ጥለው መውጣታቸው ከተሰማ ከሰዓታት በኋላ ነው።

ፕሬዚዳንቱና ባለቤታቸው በአየር ኃይል አይሮፕላን ወደ ማልዲቭስ መወሰዳቸውን የስሪላንካ አየር ኃይል አስታውቋል።

ፕሬዚዳንቱ ሥልጣናቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ዊክሬሜሲኒግሄ ማስረከባቸውን የስሪላንካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG