በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ አትሌቶች በሉዊዝያና ድል ተቀዳጁ


በቦስተን ማራቶን ኬንያዊው ጄፍሪ ሙታዪ በማራቶን አዲስ የዓለም ክብረወሰን አላስመዘገበም፥ የተያዘለት በፈጣን ጊዜ ብቻ ነው ተባለ።

በሉዊዝያናው አሥር ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር በሴቶች ውዴ አያሌው፥ 31 ደቂቃ ከ 24 ሴኮንድ በሆነ ጊዜ ቀድማ ገብታለች። በወንዶቹ አትሌት በለጠ አሰፋ 28 ደቂቃ ከ 14 ሴኮንድ ወስዶበታል።

በለጠ በውድድሩ የተሳተፉትን 8 ኬንያውያን ብቻውን ተፋልሞ ባሸናፊነት መፈጸሙ፥ ተመልካቹንና ዜና ዘጋቢዎችን አስደንቋል።

በሌላ በኩል ባለፈው ሣምንት በቦስተን ማራቶን ኬንያዊው ጄፍሪ ሙታዪ በማራቶን አዲስ የዓለም ክብረወሰን አላስመዘገበም፥ የተያዘለት በፈጣን ጊዜ ብቻ ነው ተባለ።

ማብራሪያ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዋና አሰልጣኝ ከዶክተር ይልማ በርታ አግኝተናል።

በእግር ኳስ ዜና፥ በእንግሊዙ ፕሪምየር ሊግና በስፔኑ ላ ሊጋ ማንቸስተር ዩናይትድና ባርሴሎና አሁንም የደረጃ ሠንጠረዡን በመምራት ላይ ናቸው።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG