(ይህ ገፅ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ኮምፕዩተርዎ ከአንድ በላይ ድምፅ ማጫወቻ አለው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ ፅሁፍ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸው፡፡)
ሦስቱ የኢትዮጵያ አትሌቶች ጥሩነሽ ዲባባ፥ ወርቅነሽ ኪዳኔና በላይነሽ ኦልጅራ ለሀገራቸው የወርቅ ሜዳልያ ያስገኙት ባስደናቂ የተቀናጀ የቡድን ሥራ በመሆኑ አስመስግኗቸዋል።
በተለይ ወርቅነሽና በላይነሽ የተፈሩትን የኬንያ ሯጮች ፈጥነው በማሯሯጥ ባያደክሙላት ኖሮ ጥሩነሽ መጨረሻው ላይ ያን ያህል የተመቻቸ ሁኔታ ልታገኝ እንደማትችል ግልፅ ሆኗል።
አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በቤይጂንግ ኦሊምፒክ የጣምራ ድል ባለቤት ናት።
በተመሳሳይ ርቀት በወንዶቹ ግን ኢትዮጵያ በአራት ኦሊምፒኮች ለ16 ዓመታት የበላይ የሆነችበትን ድል ቤጅንግ ላይ ተነጥቃለች።
ወንድማማቾቹ ቀነኒሣና ታሪኩ በቀለ በለንደን ኦሊምፒክ ክብሩን ለማስቀጠል ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካላቸውም።
ታሪኩ በሦስተኛነት ጨርሷል።
ኢትዮጵያ የምትታወቅበትን ማራቶን ደግሞ በሴቶቹ አሸንፋ ተገቢ ድርሻዋን መልሳለች።
ጢቂ ገላና በሩጫው መሃል ወድቃ፤ አበቃላት ሲባል ተነስታ በመሮጥ ድል ተቀዳጅታለች።
ጢቂ ዝናብ ባልተለየው የሎንዶን ማራቶን ያሸነፈችው የኦሊምፒኩን ሬከርድ በማሻሻል ጭምር ነው።
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ፡፡
(ገፁ ሲከፈት የተደራረቡ ወይም የተረበሹ ድምፆችን የሚሰሙ ከሆነ ከዚህ ሥር ካሉት ማጫወቻዎች አንደኛውን ብቻ አስቀርተው ሌሎቹን ያቁሟቸውና የሚጫወተውን እንደገና ያስጀምሩት፡፡ )