በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቅዳሜና እሁድ በተከናወኑ የበርሊንና የፕራግ ግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድሮች የኬንያና የኢትዮጵያ አትሌቶች ቀዳሚውን ሥፍራ ወሰዱ።


በትላንቱ የበርሊን ግማሽ ማራቶን የተካበተ ልምድና ዝና ያላቸውን የዕድሜ ታላላቆቹን አስከትሎ ያሸነፈው ወጣት 18 ዓመት ያልሞላው Geoffrey Kiptang የተባለ ወጣት ነው። 1 ሰዓት ከ 38 ሴኰንድ ወስዶበታል ርቀቱን ለመሸፈን።

በሴቶቹም ድሉ ከኬንያ አላለፈም። Valentina Kipketro ኢትዮጵያዊቷን ፋጤ ቶላን በሁለተኝነት አስስከትላ አሸንፋለች።

ቅዳሜ እለት ፕራግ ውስጥ በተካሄደውም ግማሽ ማራቶን በሁለቱም ፆታ ያሸነፉት የኬንያ አትሌቶች ሲሆኑ ሁለተኝነቱን ኢትዮጵያውያን አስጠብቀዋል።

Philimmo Limmo በወንዶቹ አንደኛ ሲወጣ አዝመራው በቀለ በሁለተኝነት ገብቷል።

በሴቶች ተመሳሳይ ርቀት ኢትዮጵያዊቷን በላይነሽ ዘመድኩንን ከአንድ ደቂቃ በላይ ቀድማ በአንደኝነት የጨረሰችው ኬንያዊት Lidia Cherone ትባላለች።

በእግር ኳስ፥ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግና በስፔን ላ ሊጋው መሪዎቹ ማንቸስተር ዩናይትድና ባርሴሎና ተጋጣሚዎቻቸው አሸንፈው የደረጃ ሠንጠረዡን አሁንም እየመሩ ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ ዌስት ሃምን 4 ለ 2 ሲረታ በእለቱ ሜዳው መልበቃ ብሎት ሲፈነጭ ያመሸው Wayne Rooney በጨዋታ፥ በቅጣት ምትና በፍፁም ቅጣት ምት ሦስት ጐሎችን አግብቷል።

በሌላ የአፍሪቃ እግር ኳስ ዜና፥ ከሁለት ሣምንታት በፊት በግብፁ ሐራዝ ኤል ሁዳድ 4 ለባዶ የተሸነፈው ደደቢት የእግር ኳስ ክለብ ቅዳሜ እለት የመልስ ጨዋታውን አዲስ አበባ ላይ አድርጐ አንድ ለአንድ ተለያይቷል። ከቀጣይ ማጣሪያ ውጭ ሆኗል።

ለ 2012 የለንደን ኦሊምፒክ የሴት ብሔራዊ ቡድኖች ማጣሪያም ተካሂዷል ትላንት በአዲስ አበባ ስታዲየም። ኢትዮጵያ የጋና አቻውን አንድ ለዜሮ አሸንፏል።የመልሱ ጨዋታ ከሁለት ሣምንት በኋላ መክራ ላይ ተካሂዶ ወደ ቀጣይ ማጣሪያ ለማለፍ ድምር ውጤታቸው ይጠበቃል።

ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG