በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳምንታዊ የስፖርት ዜና


በኒውዮርኩ Diamond League ደጀን ገብረመስቀል ታሪክ ሠራ

ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ እዚህ በዩናይትድ ስቴትስ ኒው ዮርክ ከተማ በተካሄደው ሁለተኛው Diamond League ጠንካራ ፉክክሮች ታይተዋል። አስገራሚ ውጤቶችና አዳዲስ ፊቶችም በአሸናፊነት ብቅ ብለውበታል።

በ 100 ሜትር የአሜሪካዊው Tyson Gay መሸነፍ ከአዳዲስ ክስተቶች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል። ሌላው አስገራሚ ክስተት በወንዶቹ 5 ሺህ ሜትር ኢትዮጵያዊው ደጀን ገብረመስቀል በመጨረሻው 400 ሜትር ላይ ያሳየው ያሯሯጥ ስልትና ያጨራረስ ብቃት ነው። በዚህ ውድድር ያሸንፋል ተብሎ ቅድሚያ ግምት የተሰጠው አሜሪካዊው Bernard Lagat ሁለተኛ ሲሆን ታሪኩ በቀለ ከኢትዮጵያ በሦስተኝነት ጨርሷል።

በሳምንቱ ማብቂያ ሌሎች የአትሌቲክስና የእግር ኳስ ውድድሮች በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ ተካሂደዋል።

ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG