በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አርባኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ።


ከክለቦች መከላከያ ባጠቃላይ ውጤት ዘንዶሮም ቀዳሚ ሆነ።

ለአምስት ቀናት ሲካሄድ የቆየው አርባኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቀቀ።

ከክለቦች መከላከያ ባጠቃላይ ውጤት ዘንዶሮም ቀዳሚ ሆነ።

በሴቶች ሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል፥ የኦርሚያዋ ሲሳይ ኰረሜ ከማሸነፍ አልፋ አዲስ ብሔራዊ ክብረወሰን አስመዝግባለች።

በዘንድሮው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በኰከብነት ከተመረጡት ሦስት አትሌቶች መካከል ባጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ መሻሻልና ለውጥ ያሳየችው የፌዴራል ማረሚያ ፖሊስ ስፖርት ክለብ ተወካይ ፋንቱ እንጌሦ በመቶ በሁለት መቶና በአራት በመቶ የዱላ ቅብብል አሸናፊ መሆኗ ተደናቂ አድርጓል። ወደፊትም ተስፋ ተጥሎባታል።

በእግር ኳስ በጀርመን ቡንደስሊጋና በኢጣልያው ሤሪ - አ የየሀገሮቹ የዓመቱ ሻምፒዮባዎች ቀደም ብለው ታውቀዋል። በተወዳጁ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ደግሞ ትላንት ቼልሲን ሁለት ለአንድ የረታው ማንቸስተር ዩናይትድ ዋንጫውን ለማንሳት መቃረቡን አረጋግጧል።

ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ

XS
SM
MD
LG