በአትሌቲክስ ስፖርት ዜና፥ በ Fukoka ጃፓን እና Singapore በሳምንቱ ማብቂያ ሁለት የማራቶን ውድድሮች ተካሂደዋል።
በእግር ኳስ የግብጹ Al Ahly ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ውድድሮች አሸንፎ ዋንጫ አነሳ። የአይቮሪ ኮስትን Sewe ስፖርት 2 ለ 1 ረትቷል። Al Ahly ከዚህ ቀደም ስምንቴ የካፍ ሊግ ሻምፒዮና፥ ስድስቴ የካፍ Super Cup ፍጻሜና አራት ጊዜ ያፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜ ውድድሮችን ያሸነፈ ሲሆን፥ ይህኛው የከትላንት በስቲያው አስራ ዘጠነኛ ድሉ ነው።