”ከተባበርን ኢቦላን እናሸንፋለን” በሚሉት አስራ አንድ የአለም ኮከብ እግር ኳስ ተጫዋቾች መካከል፥ የ Real Madridዱ Christiano Ronaldo, የባርሴሎናው Neymar Jr., የቼልሲው Didier Drogba እና የባየርን ሙኒኩ፥ Philipp Lahn ይገኙበታል። በዚህ “11 Against Ebola” በተሰኘ አዲሱ ጸረ-ኢቦላ ዘመቻቸው፥ የኮከብ እግር ኳስ ተጫዋቾቹ ትኩረት፥ በየማህበረሰቡ እየዞሩ፥ የበሽታውን ስርጭት መከላከል ስለሚያስችሉ እርምጃዎች ግንዛቤ መስጠት ነው።
በምሽቱ የስፖርት ቅንብር፥ የኢትዮጵያ አትሌቶች በ Atapuerca አገር አቋራጭ ሩጫ ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ያሸነፉበት፥
በኢስታንቡል ማራቶን ድል የተቀዳጁበትና የእግር ኳስ ስፖርት ዜናዎች ፍቅሩ ኪዳኔም የኬንያ አትሌቶችን የጉልበት ሰጪ መድሃኒት መጠቀም አስመልክቶ አስተያየታቸውን ያጋራሉ።