ኢትዮጵያና ቤኒን ባዶ ለባዶ በተለያዩበት የአዲስ አበባው ግጥሚያ፥ እንግዳው ቡድን በመከላከል ጀምሮ በመከላከል ጨርሷል። ከመቼውም በበለጠ እንቅስቃሴ ያደረገው የኢትዮጵያ ቡድን ከአራት ያላነሱ ግቦች ስቷል።
በማራቶን ለመጀመሪያ ጊዜ የሮጠው ኬንያዊ ሣሙኤል ንዱንጉ የገባበት ሰዓትም ድንቅ ነው። 2 ሰዓት 7 ደቂቃ 04 ሴኮንድ አስመዝግቧል።
የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ-አንድ፥ የመጀመሪያ ዓመታዊ በዓሉን ከሰኔ 24 - 29 እንደሚያስተናግድ አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን ጨምሮ በተለያዩ ክለቦች በአጥቂ መሥመር ተሰላፊና አሰልጣኝ ሕሩይ ንጋቱ በ 64 ዓመቱ ድንገት አረፈ።
ዝርዝሩን ከዘገባው ያዳምጡ።