ዋሽንግተን፡አዲስ አበባ —
በአትሌቲክስ በኢብራሂም ጄላን የተመራው ጠንካራ የኢትዮጵያ ቡድን ስቶክሆልም ስዊድን ላይ በተካሄደው ዳያመንድ ሊግ በ 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ተከታትሎ በመግባት ታሪክ አስመዘገበ።
በዩናይትድ ስቴትስ የክሊቭላድ ካሊቨርስ ቲም ጎልደን ስቴትስ ዎርየርስን 93 ለ 89 በማሸነፍ የዘንድሮውን የብሄራዊ ቅርጫት ኳስ ዋንጫ ወሰደ።
ላለፉት 52 ዓመታት ዋንጫ ተጠምቶ የቆየው የክሊቭላድ ካሊቨርስ ቲም ትላንት ዋንጫ ሲያነሳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው። የትላንቱ ድል ለከተማዋ ብቻ ሳይሆን ለኮከብ ተጫዋቿ ለሌብሮን ጄምስ ጭምር ነው።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።