በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ መንግሥትን የሚቃወሙ ሰልፎች ቀጥለዋል


በኬንያ መንግሥትን የሚቃወሙ ሰልፎች ቀጥለዋል
በኬንያ መንግሥትን የሚቃወሙ ሰልፎች ቀጥለዋል

ግጭቱ ተባብሶ ወደ 2007ቱ ዓይነት እልቂት እንዳያመራ አስግቷል

በኬንያ፣ እየናረ በመጣው የኑሮ ውድነት ሳቢያ መንግሥትን በመቃወም፣ ዛሬ ለሦስተኛ ቀን በአንዳንድ ቦታዎች በቀጠለው ሰልፍ፣ ከፖሊስ ጋራ የተደረጉ ግጭቶች ታይተዋል።

ባለፈው ሰኞ በነበረው ሰልፍ በተፈጠረው ከበድ ያለ ግጭት ምክንያት፣ በዛሬው ሰልፍ፣ የፖሊስ ኃይል ልዩ የግጭት መከላከያ መሣሪያዎችን ይዞ ተስተውሏል፡፡

ማታሬ እና ኪቤራ በተሰኙትና በርካታ ሰዎች በሚኖሩባቸው የናይሮቢ መንደሮች፣ ሰልፈኞች፣ በፖሊስ ላይ ደንጊያ ወርውረዋል፤ ጎማ አቃጥለዋል፡፡ ፖሊስ በምላሹ፣ አስለቃሽ ጋዝ ተኩሷል፡፡

በምዕራብ ኬንያ የተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ ጠንካራ ደጋፊዎች በሚገኙባቸው፣ ኪሱሙ እና ሆማ ቤይ፣ ተቃዋሚዎች በፖሊስ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩ እና መሀል መንገድ ላይ እሳት ሲያቃጥሉ ውለዋል፡፡ ኹኔታው ለቀማኞችም አመቺ በመኾኑ፣ ዘረፋ በብዛት ተስተውሏል፡፡

ተቃዋሚው ራይላ ኦዲንጋ፥ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት፣ ባለፈው ዓመት የተደረገውን ምርጫ አጭበርብረዋል፤ እንዲሁም፣ የኑሮ ውድነቱን ማስተካከል አልቻሉም፤ በሚል፣ በየሳምንቱ ሰኞ እና ኀሙስ ሰልፍ እንዲደረግ ጥሪ አድርገዋል፡፡

መንግሥት ሰልፎቹ፣ “ሕገ ወጥ ናቸው፤” ይላል፡፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የሃይማኖት ቡድኖች ደግሞ፣ ኹኔታዎች ተባብሰው እአአ በ2007 ከተደረገው ምርጫ በኋላ ወደተከሠተው የጎሣ ግጭት ዓይነት እንዳያመራ ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ በዚያ ዓመት አጋጥሞ በነበረው ብጥብጥ፣ 1ሺሕ100 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG