በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ


አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን
አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን

ለ250 ሺህ ዜጎች የሚሆን ሰብአዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታውቋል።

ሰብአዊ ድጋፉን የሚያስተባብሩ ቡድኖች መሰማራታቸውንም አመልክቷል። የሰብአዊ ድጋፍ እንቅስቃሴው የሚመራው በኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን የገለፁት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ፍሰት ቃል አቀባይ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ ሌሎች የሰብአዊ ድጋፍ ተቋማት የመንግሥትን መመሪያዎች እና የአገሪቱን ሕግ አክብረው እንዲሳተፉ አሳስበዋል።

ትግራይ ውስጥ ወደሚገኘው ሽመልባ የስደተኞች መጠለያ እያተጓዙ እንደነበር የገለጹ የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች ተኩስ ያጋጠማቸውም ሁለት ኬላዎችን ከጣሱ በኋላ ሦስተኛውንም ሊጥሱ ሲሉ መሆኑን አምባሳደር ሬድዋን ተናግረዋል።

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር በሚገኙት የህወሃት ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም እንደዚሁም በቀድሞው የትግራይ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አምባሳደር አዲስ አለም ባሌማ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አመልክተዋል::

“በሽሽት ላይ ካሉት የህወሓት መሪዎች አብዛኛዎቹም በጥቂት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ተይዘው ለፍርድ ይቀርባሉ” ብለዋል አምባሳደር ሬድዋን።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል መላኩን የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00


XS
SM
MD
LG