በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፌልትማን እና ጉቴሬዥ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ መከሩ


የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ
የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፌልትማን እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ ትናንት ረቡዕ በዋና ጸኃፊው ጽህፈት ቤት ተገኛኝተዋል።

ሁለቱ ባለሥልጣናት የተገናኙት እየተበላሸ መጥቷል ባሉት የኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ ለመነጋገር መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው ቃል አሳውቋል።

የንግግራቸው አጀንዳም በድርድር ላይ የተመሰረተ ተኩስ አቁም መድረስን አጣዳፊነት እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ባልተገደበ ሁኔታ እንዲደርስ ማድረግ አስፈላጊነት ላይ እንደነበረ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG