ዋሺንግተን ዲሲ —
የሶማልያ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሞሐመድ ኡስማን ጃዋሪ ከሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ለሦስት ሳምንታት ያህል የሥልጣን ትግል ሲያካሄዱ ከቆዩ በኋላ ከሥልጣን መሰናበታቸውን ተነገረ።
የህገ-መንግስት ሚኒስትር አብዲራሕማን ሆሽ ጂብሪል አፈ-ጉባዔ ጃዋሪ ከሥልጣን የመሰናበት ደብዳቤ አቅርበዋል ሲሉ በትዊተር አስታውቀዋል። የምክር ቤት አባል ሑሴን አረብ ኢሴም አፈ ጉባዔው ከሥልጣን እንደተሰናበቱ የአሜሪካ ድምፅ የሶማልኛ አገልግሎት ተናግረዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ