በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስፔን የባህር ወሰን ጠባቂዎች 181 ፍልስተኞችን አዳኑ


የስፔን የባህር ወሰን ጠባቂዎች 181 ፍልስተኞችን አዳኑ
የስፔን የባህር ወሰን ጠባቂዎች 181 ፍልስተኞችን አዳኑ

የስፔን የባህር ወሰን ጠባቂዎች ካለፈው እሁድ ጀምሮ በካናሪ ደሴቶች አቅራቢያ በሚገኘው ባህር ላይ በአራት የተለያዩ ጀልባዎች የነበሩትን 181 ፍልስተኞችን ማዳናቸውን የካናሪ ደሴቶች የአስቸኳይ አገልግሎት ዛሬ ሰኞ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የነፍስ አድን መርከቦቹ 42 ወንዶችና 9 ሴቶችን በድምሩ 51 ፍልስተኞችን፣ ግራን ካናሪያ በተባለው ደሴቶች ወደሚገኘው የአርጉዊንጉዊን ወደብ እንደወሰዷቸው ተገልጿል፡፡

ፍልሰተኞቹ የተገኙት ከተባለው አካባቢው 100 ማይል ርቀት ላይ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ከሌሎች ሦስት ጀልባዎች የተገኙ 130 የሚደርሱ ፍልሰተኞችም ላንዞሮቴ በተባለችው ደሴት ወደሚገኘው ላ ሴቦላ ወደብ መጓጓዛቸው ተመልክቷል፡፡

በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልሰተኞች የተሻለ ህይወት ፍለጋ ከሰሜን አፍሪካ ባህር አቋርጠው ወደ አውሮፓ እንደሚሰደዱ ተነግሯል፡፡

የስፔን አገር ውስጥ ሚኒስቴር መረጃ እንደሚያሳየው ባላፈው የጥር ወር ውስጥ ብቻ 566 ፍልሰተኞች የካናሪ ደሴቶችን በጀልባ አቋርጠው ሄደዋል፡፡

እኤአ ባለፈው 2022 ውስጥ 15ሺ682 ፍልስተኞች የካናሪ ደሴቶች ማቋረጣቸው ሲነገር፣ ከሱ ቀደም ሲል ከነበረው የ2021 ጋር ሲነጻጸር የ29.7 ከመቶ ቅናሽ ማሳየቱም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG