በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በስፔን የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 51 ሰዎች መሞታቸውን ባለሥልጣናት አስታወቁ


የጎርፍ አደጋው ከደረሰ በኋላ ተሽከርካሪዎች በጎርፉ ተጠራርገው ይታያሉ፤ ቫሌንሲያ፤ ስፔን
የጎርፍ አደጋው ከደረሰ በኋላ ተሽከርካሪዎች በጎርፉ ተጠራርገው ይታያሉ፤ ቫሌንሲያ፤ ስፔን

ትላንት ማክሰኞ ዕለት በደቡብ እና ምስራቅ የስፔን አካባቢዎች የጣለው አውሎ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ ባስከተለው ድንገተኛ ጎርፍ የ51 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የስፔን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

አውሮፓ ውስጥ በቅርብ ጊዜ ተከስቶ የማያውቅ የከፋ የተፈጥሮ አደጋ መሆኑ የተገለጸው ይህ ጎርፍ መኪናዎችን ጠራርጎ መውሰዱን፣ አውራ ጎዳናዎችን ወደ ወንዝነት መቀየሩን እና የባቡር መሥመሮችን ማስተጓጎሉንም አመልክተዋል።

ማላጋ በተሰኘው ከተማ አቅራቢያ 300 ሰዎችን አሳፍሮ በፍጥነት ይጓዝ የነበረ ባቡርም ከመስመር ውጪ የወጣ ሲሆን የተጎዳ ሰው ግን እንደሌለ ባለሥልጣናቱ አመልክተዋል። በፍጥነት የሚጓዘው የጭቃ ቀለም ያለው የጎርፍ ውሃ መኪናዎችን እያላጋ ሲወስድም ታይቷል።

ፖሊስ እና የነፍስ አድን አገልግሎት ሠራተኞች ሄሊኮፕተሮችን በመጠቀም ሰዎችን ከቤታቸው እና ከመኪናዎቻቸው ያወጡ ቢሆንም በርካታ ሰዎች እስካሁን የደረሱበት እንደማይታወቅ ባለሥልጣናቱ ማክሰኞ ማታ አስታውቀው ነበር።

የስፔን የአደጋ ጊዜ ምላሽ አባል የሆኑ ከ1ሺህ በላይ ወታደሮች በአደጋው ወደተጎዱ አካባቢዎች ተሰማርተው ፍለጋ በቀጠሉበት ወቅት፣ የሟቾቹ ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል የሚል ስጋት እንዳለ ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG