በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስፔን 6መቶ ፍልሰተኞች መቀበሏን አስታወቀች

ስፔን 6መቶ ፍልሰተኞች የሚገኙባትንና ተቀባይ አጥታ አጣብቂኝ ውስጥ የነበረችዋን መርከብ ዛሬ መቀበሏን አስታወቀች። ቀደም ሲል ጣልያንና ማልታ መርከቢቷን ለመቀበል እንዳልፈለጉም ተመልክቷል።

ስፔን 6መቶ ፍልሰተኞች የሚገኙባትንና ተቀባይ አጥታ አጣብቂኝ ውስጥ የነበረችዋን መርከብ ዛሬ መቀበሏን አስታወቀች። ቀደም ሲል ጣልያንና ማልታ መርከቢቷን ለመቀበል እንዳልፈለጉም ተመልክቷል።

ወደ ሥልጣን ከመጡ ገና አንድ ሳምንት የሆናቸው የስፓኙ ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዚ ፣ መርከቧ በበቫልንሲያ ምሥራቃዊ ወደብ ላይ እንድትቆም መመሪያ መስጠታቸውን፣ ከቢሯቸው የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

አንድ የጀርመን የበጎ፡አድራጊ ድርጅት እንዳስታወቀው፣ መጀመሪያ ወደ ፻ ያህል ህፃናት የሚገኙባቸው 629 ሰዎች ነበሩ ከሊብያ ወደ ጣልያን ያመሩት።

ይሁንና የጣልያኑ አገር አሰተዳደር ሚኒስትር ማትተኦ ጻልቪኒ መርከቧ ወደ አገራቸው እንዳትገባ በማገዳቸው ፍልሰተኞቹ አንድ ሙሉ ቀን ወደቡ ላይ እንዲቆዩ ተገደው ነበር።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG