በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያደረገችው ሥምምነት


ብሪታንያና ስፓኝ በብሪታንያ ቅኝ ግዛት ጂብራልታር ላይ ያላቸው ለምዕተ ዓመታት ያህል የዘለቀ ጠብ በብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣት ሂደት ላይ የጠብ ስጋት አሳድሯል።

ብሪታንያና ስፓኝ በብሪታንያ ቅኝ ግዛት ጂብራልታር ላይ ያላቸው ለምዕተ ዓመታት ያህል የዘለቀ ጠብ በብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣት ሂደት ላይ የጠብ ስጋት አሳድሯል።

ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያደረገችው ሥምምነት በመጪው እሁድ በሚካሄደው የአውሮፓ ኮሚሽን ስብስባ ላይ ድምፅ ይሰጥበታል።

የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትርና ከፍተኛ ዲፕሎማቶቻቸው የብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣትን አስመልክቶ የረቀቀው የሥምምነት ሃሳብ ማድሪድ በጂራልታር ላይ ያላትን የመወሰን ሚናን ችላ ብሏል በሚል አውግዘውታል።

የጂብራልታር ዋና ሚኒስትር ፋብያን ፒካርዶ ዛሬ ሥምምነት የተደረገው ከስቴን ባለሥልጣኖች ጋር ለመመካከር ወደ ማድሪድ በሄድኩበት ወቅት ነው ሲሉ በብሪታንያ የዜና ስርጭት ኮርፖሬሽን ተናግረዋል። የስፔን የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር በበኩላቸው ፒካርዶ የሚናገሩት በግበርና በድንበር ጉዳይ ስለሚደረገው ቴክኒካዊ ድርድር ነው። ሆኖም ገና ያልተፈቱ ወሳኝ ልዩነቶች አሉ ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG