በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ስፓኝ ከካናሪ ደሴቶች ከሚጎርፈው ፍልሰተኛ መሃል የሆኑ 114 ሰዎችን ሕይወት ከአደጋ ታደገች

የስፓኝ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ትላንት ምሽት ከካናሪ ደሴቶች አቅራቢያ ባሕር ላይ ያገኟቸውን 114 ስደተኞች በሕይወት ታድገው በግራን ካናሪያ ደሴት ከሚገኘው የአርጊኔጊን ወደብ አደረሱ።

ከግራን ካናሪያ በስተደቡብ ስምንት ማይሎች ርቀት ላይ የተገኘችው የእንጨት ጀልባ ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉት የአፍሪቃ አገራት የመጡ ስደተኞችን አሳፍራ እንደነበር ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

የስፓኝ የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር መረጃ በትላንትናው ዕለት ይፋ እንዳደረገው፡ በያዝነው የአውሮፓውያኑ 2023 የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት ውስጥ ብቻ ከአትላንቲክ ውቅያኖሶቹ የካናሪ ደሴቶች የደረሰው ቁጥሩ 30, 705 የሚደርሰው ስደተኛ አሃዝ በ2006 ሙሉ ዓመት የተዘገበውን ሪከርድ ተቃርቧል።

ከአፍሪቃ ተነስተው አደገኛውን ባሕር አቋርጠው የመጡት ሰዎች ቁጥር ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በ111 በመቶ መጨመሩን ያመለከተው መረጃ፣ ስፓኝ ወደብ ከደረሰው ከአጠቃላዩ አሃዝ 43, 290 የሚጠጋ ስደተኛ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ ነው። በባሕር ተጉዞ ስፓኝ የገባው አጠቃላይ ፍልሰተኛ ቁጥርም ካለፈው ዓመት በ66 በመቶ መጨመሩን መረጃው አክሎ ጠቁሟል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG