በካናሪ ደሴቶች የባሕር ዳርቻ ይጓዙ በነበሩ በርካታ ጀልባዎች ተሳፍረው የነበሩ ስድስት ስደተኞች ሞተው መገኘታቸውን የስፔይን የድንገተኛ አደጋ አገልግሎት ዛሬ ረቡዕ አስታወቀ፡፡
የስደተኞቹ አስከሬኖች የተገኙት የነፍስ አድን ሠራተኞች በሰሜን ምዕራብ አፍሪካ የባሕር ዳርቻ ከሚገኙ ደሴቶች ትንሿ በሆነችው በኤል ሃይሮ አቅራቢያ አራት ጀልባዎችን በያዙብት ወቅት ነው፡፡
አንደኛው ጀልባ ወደ ወደቡ ለመድረስ የቻለ ሲኾን አራት ሰዎች መሞታቸው ሊረጋገጥ ችሏል፡፡ አምስተኛ ሰው በልብ ድካም ሕይወቱ ማለፉ ተረጋግጧል፡፡ ስድስተኛ ሰው ከሦስቱ ጀልባዎች በአንደኛው ውስጥ ሞቶ እንደተገኘ፣ የነፍስ ቡድኑ ኤክስ ላይ ባወጣው መልዕክት አስታውቋል፡፡
ጀልባዎቹ ላይ ምን ያህል ሰዎች ተሳፍረው እንደነበር አልተገለጸም፡፡ በካናሪ ደሴቶቹ በኩል አቋርጠው ወደ ስፔይን የሚደርሱ ህገ ወጥ ፍልሰተኞች ቁጥር ከቅርብ ወራት ወዲህ እየጨመረ መሆኑ ተገልጿል፡፡
የስፔይን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደገለጸው ካለፈው ጥር እስከ ህዳር መጨረሻ በነበረው ጊዜ 41,425 ፍልሰተኞች ደሴቶቹ ላይ ደርሰዋል፡፡ ባለፈው ዓመት በጠቅላላው ከነበረው 39 ሺሕ 910 ጋራ ሲነጻጸር ከፍተኛ ለውጥ ማሳየቱ ተመልክቷል።
በቅርብ ዓመታት ከአፍሪካ እየተነሱ በአትላንቲክ አደጋዎች ውቅያኖስ መሸጋገሪያ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት የሞክሩ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በተደጋጋሚ በደረሱ የጀልባ መገልበጥ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
መድረክ / ፎረም