ዋሽንግተን ዲሲ —
የህወሓት ታጣቂዎች ደቡብ ወሎ ዞን ውስጥ በቆዩበት ጊዜ “548 ሲቪሎችን ገድለዋል፤ ቢያንስ 217 ሴቶችን ደፍረዋል” ሲሉ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ክስ አሰምተዋል።
ታጣቂዎቹ “በተቋማት ላይ አደረሱት” ባሉት “ዘረፋና ውድመት”ም ከ47.6 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት መድረሱን ያመለከቱት ዋና አስተዳዳሪው አብዱ ሁሴን ለመንግሥት፣ መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማትና ከሃገር ውጭ ለሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ባስተላለፉት መልዕክት መልሶ ማቋቋምና በልማት እንቅስቃሴዎች ውስጥ እንዲሳተፉ ጠይቀዋል።
አኀዞቹ የወጡት የመጀመሪያ የዳሰሳ ጥናቶችን መሠረት አድርገው መሆኑን አስተዳዳሪው ጠቁመው የጉዳቱ መጠንም ሆነ የተጎጅዎቹ ቁጥር ከተጠቀሰው በላይ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ህወሓት የሚነሱበትን የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችና በሲቪል ተቋማት ላይ ተፈፅመዋል የተባሉ ጥቃቶችና ውድመትን በተደጋጋሚ ሲያስተባብል መቆየቱ ይታወቃል።
ዝርዝሩ ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ።