በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው አደጋ ስድስት ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ


በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኘው ደቡብ ቤንች ወረዳ እና በምዕራብ ኦሞ ዞን በሚገኘው ጋችት ወረዳ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኘው ደቡብ ቤንች ወረዳ እና በምዕራብ ኦሞ ዞን በሚገኘው ጋችት ወረዳ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኘው ደቡብ ቤንች ወረዳ እና በምዕራብ ኦሞ ዞን በሚገኘው ጋችት ወረዳ ረቡዕ መስከረም 29 ቀን 2017 የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው አውሎነፋስና የጎርፍ አደጋ ስደስት ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በቤንች ሸኮ ዞን፣ ደቡብ ቤንች ወረዳ፣ በርታ ቀበሌ፣ በዕለቱ አውሎ ንፋስ ቀላቅሎ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው አደጋ ሶስት ሰዎች ሲሞቱ ስምንት ሰዎች ከባድ እና ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ቃል አቀባይ ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዝናቡን ተከትሎ በመኖሪያ ቤት ላይ የወደቀ ዛፍ የሁለት ወር አራስ የሆነች እናትና ልጇን ጨምሮ የሦስት ሰዎች ሕይወት አጥፍቷል ሲሉ ቃል አቀባዩ አስረድተዋል ።

በተመሳሳይ ቀን ማለትም ረቡዕ መስከረም 28 ቀን 2017 በክልሉ ምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ጋችት ወረዳ፣ ቱልት ቀበሌ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተ ጎርፍ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን እና የሁለቱ አስከሬን መገኘቱን አክለው ተናግረዋል።

ባለፈው ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ/ም በአከባቢው የጣለው ተመሳሳይ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ስደስት ሰዎች መገደላቸውን የአሜሪካ ድምፅ መዘገቡን የዮናታን ዘብዲዮስ ዘገባ አስታውሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG