በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሪያክ ማቻር ከደቡብ አፍሪካ ጁባ ገቡ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

የደቡብ ሱዳን አማፅያን መሪ ሪያክ ማቻር በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ በጦርነት ወደ ደቀቀቸው መዲና ተመልሰዋል።

የደቡብ ሱዳን አማፅያን መሪ ሪያክ ማቻር በሁለት ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ በጦርነት ወደ ደቀቀቸው መዲና ተመልሰዋል።

ማቻር ዛሬ ከደቡብ አፍሪካ ጁባ የገቡት በተቀናቃኛቸው የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር አስተናጋጅነት በተደረገ ሥነ ሥርዓት ለመሳተፍ ነው። ሁለቱ ሰዎች በደቡብ ሱዳን ለአምስት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ የተከሄደውን የእርስ በርስ ጦርነት ለማቆም ባለፈው መስከረም ወር የሰላም ሥምምነት ፈርመው ነበር።

ደቡብ ሱዳን ከሰባት ዓመታት በፊት ከሱዳን ተገንጥላ ነፃ ሀገር በሆነችበት ወቅት ማቻር ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገላቸው የሚታወስ ነው። ይሁንና በፕሬዚዳንት ሳል ቫኪርና በማቻር መካከል በተከሰተው የሥልጣን ሽምያ ምክንያት በሁለቱ ባለሥልጣኖች ተከታዮች መካከል ውጊያ አስከተለ። ከዚያ በኋላ ኪርና ማቻር በርካታ የሰላም ሥምምነቶች አድርገዋል። ነገር ግን ሁሉም ከሽፈዋል።

ውጊያው በመቀጠሉ ወደ 400,000 የሚጠጉ ደቡብ ሱዳናውያን ህይወታቸውን አጥተዋል። በሚሊዮኖቹ የሚቆጠሩት ደግሞ ከመኖርያቸው ተፈናቅለዋል።

በወቅቱ የሰላም ሥምምነት መሰረት ማቻር በብሄራዊ ውኅደት መንግሥት ውስጥ ከአምስት ምክትል ፕሬዚዳንቶች ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ይሆናሉ።

ሪያክ ማቻር ከደቡብ አፍሪካ ጁባ ገቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:10 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG