በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሳልቫኪርና በተቀናቃኛቸው ሪያክ ማቻር መካከል ተፈርሞ የነበረው ተኩስ ማቆም

በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና በተቀናቃኛቸው መካከል ሰሞኑን ተፈርሞ የነበረው ተኩስ የማቆም ሥምምነት ተግባራዊ በሆኑ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ትናንት መጣሱ ተገልጿል፡፡

በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪርና በተቀናቃኛቸው መካከል ሰሞኑን ተፈርሞ የነበረው ተኩስ የማቆም ሥምምነት ተግባራዊ በሆኑ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ትናንት መጣሱ ተገልጿል፡፡

የአማፂያኑ ቃል አቀባይ አቶሚ ዋክ አቶኒ የመንግሥት ኃይሎች ሞዩ በምትባል የሰሜን ምዕራብ ይዞታቸው ላይ ጥቃት ከፍተዋል ሲሉ ከስሰዋል፡፡

ጥቃቱ የተከፈተው ሰምምነቱ ተፈፃኒ መሆኑ በጀመረ በስድሰት ሰዓታት ዕድሜ ውስጥ መሆኑም ጠቁመዋል፡፡

የመንግሥቱ ቃል አቀባይ አቶኒ ዋክ አቶኒ ለአሶሼየትድ ፕሬስ የዜና አውታር በሰጡት ቃል “የላላ አመራር ያላቸው፤ ማንነት የማይቆጣጠራቸው” ያሏቸው ተቃዋሚዎች ጥቃት መክፈታቸውን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ሳልቫኪርና የቀድሞ ምክትላቸው የዛሬ የአማፂያኑ መሪ ሪያክ ማቻር ስምምነቱን የፈረሙት ካርቱም ላይ ግንባር ለግንባር ተገናኝተው ከተነጋገሩ በኋላ ባለፈው ረቡዕ እንደነበር ይታወቃል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG