በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ሴት መሪዎች

የደቡብ ሱዳን ሴት መሪዎች በቅርቡ በተደረገው የሰለም ሥምምነት መሰረት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ከከፍተኛ ሥልጣን ሹመቶች 35 ከመቶዎቹ ለሴቶች እንዲመድቡ ጥሪ አድርገዋል።

የደቡብ ሱዳን ሴት መሪዎች በቅርቡ በተደረገው የሰለም ሥምምነት መሰረት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ከከፍተኛ ሥልጣን ሹመቶች 35 ከመቶዎቹ ለሴቶች እንዲመድቡ ጥሪ አድርገዋል።

ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የደቡብ ሱዳን የሽግግር መንግሥት የመመስረቱን ሂዳት ለመጀመር ባለፈው ማክሰኞ አሥር ሰዎችን ያቀፈ ኮሚቴ መስርተዋል። ከአሥሩ ሰዎች ታድያ አንድ ሴት ብቻ ነው ያሉት።

ለሴቶች የተመደበው ጣርያ አለመከበሩ እንዳላስደሰታቸው ሜሪ አየን ማጆክ የተባሉ የሽግግር ምክር ቤት አባል ትላንት ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ሬጂና ጆሴፍ ካባ የቀድሞው የሱዳን ህዝባዊ ሃርነት የፖለቲካ እስረኞች አንጃ ንቅናቄ ተወካይ ናቸው። ቡድኑ በአዲስ አበባ የተደረገውን ሥምምነት ከፈረሙት አካላት አንዱ ነው። የፆታ ሚዛን የመጠበቁ ጉዳይ የማያቋርጥ ትግል ነው። ኮሚቴውም በአዲስ አበባ የተደረሰውን ሥምምነት አልተከተልም ሲሉ አማረዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG