በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን የምግብ ችግር ይዞታ እየተባባሰ ነው

የደቡብ ሱዳን የምግብ ችግር ይዞታ እየተባባሰ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ የሠብዓዊ ረድዔት ድርጅቶችና የሀገሪቱ መንግሥት ያወጡት አዲስ ሪፖርት ገለጠ።

የደቡብ ሱዳን የምግብ ችግር ይዞታ እየተባባሰ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የተለያዩ የሠብዓዊ ረድዔት ድርጅቶችና የሀገሪቱ መንግሥት ያወጡት አዲስ ሪፖርት ገለጠ።

ባለፈው ሰኔ ወር ሥድስት ሚሊዮን የነበረው ለከባድ የምግብ እጥረት የተጋለጡት ሰዎች ቁጥር በዚህ የአውሮፓውያን ዓመት የመጨረሻው ሩብ ወደ አራት ነጥብ ሥምንት ሚሊዮን እንደሚቀንስ ሪፖርቱ ተንብያል።

ይሁን እንጂ የመኸር መሰብሰቢያው ወቅት እየጀመረ ባለበት ባሁኑ ወቅት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በአንድ ነጥብ አራት ሚሊዮን ተጨማሪ ሰዎች የዕለት ጉርሳቸውን ከየት እንደሚያገኙ የማያውቁበት ሁኒታ ላይ እንዳሉ ሪፖርቱ አመልክቷል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG