በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሥር የደቡብ ሱዳን ወታደሮች የወሲብ ጥቃትና ግድያ ፈፅመዋል በሚል ክስ ተፈርደባቸው


አሥር የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ከሁለት ዓመታት በፊት አንድ ሆቴል ውስጥ ወረራ ባካሄዱበት ወቅት የወሲብ ጥቃትና ግድያ ፈፅመዋል በሚል ክስ ተፈርዶባቸዋል።

አሥር የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ከሁለት ዓመታት በፊት አንድ ሆቴል ውስጥ ወረራ ባካሄዱበት ወቅት የወሲብ ጥቃትና ግድያ ፈፅመዋል በሚል ክስ ተፈርዶባቸዋል።

ካች አምና ከአምሳ እስከ መቶ የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች በሀገሪቱ መዲና ጁባ የሚገኘውን ተረይን የተባለውን ሆቴል በወረሩበት ወቅት አንድ የሀገሪቱ ጋዜጠኛ እንደተገደለና አምስት የዓለምቀፍ ረድዔት ሠራተኞች ላይ ከባድ የኅብረት የወሲብ ጥቃት እንደተፈፀማባቸው የሆቴሉ አስተዳዳሪ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። አንድ አሜሪካዊ የረድዔት ሠራተኛም ተተኩሶበት ቆስሎ ነበር።

ወታደሮቹ ከሰባት ዓመታት እስከ ዕድሜ ይፍታህ እስራት ተፈርዶባቸዋል። መንግሥት ለእያንዳንዳቸው የፆታ ጥቃት ሰለባዎች 4ሺህ ዶላር እንዲከፍል ተበይኗል። ለሆቴሉ ባለቤት ደግሞ መንግሥት ከ2 ሚልዮን ዶላር በላይ እንዲከፍለው ተበይኗል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG