በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንት ለኮቪድ-19 መጋለጣቸው ተገለፀ


ፎቶ ፋይል ፥ ጄምስ ዋኒ ኢጋ
ፎቶ ፋይል ፥ ጄምስ ዋኒ ኢጋ

ለበርካታ ዓመታት በደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዚዳንትነት የቆዩት ኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው ተዘገበ።

ጂምስ ዋኒ ኢጋ ለመንግሥታዊው ደቡብ ሱዳን ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በሰጡት መግለጫ የምርመራ ውጤቴ፣ ለቫይረሱ የተጋለጥኩ መሆኔን ያሳያል ብለዋል፤ ከጥቂት ቀናት በፊት ነው ናሙናየ ለምርመራ የተወሰደው፣ዛሬ ውጤቱ ኮሮና አሳይቷል፤ ደቡብ ሱዳናውያን ሁሉ እንዲመረመሩ አበረታታለሁ፤ ምክንያቱም በሽታው እንዳይዛመት ለመከላከል በጅጉ አስፈላጊ ስለሆነ ብለዋል።

የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ላይ ቫይረሱ በምርመራ ሲገኝ ምክትል ፕሬዚዳንቱ አምስተኛ መሆናቸው ነው፤ የአዲሱ የደቡብ ሱዳን ፀረ ኮቪድ-19 ሊቀመንበር ሆነው የተሾሙት አምስተኛው የሃገሪቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሲአን አብደልባጊ ባለፈው ሳምንት በምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘላቸው አይዘነጋም።

ተቀዳሚ ምክትል ፕረዚዳንቱ ሪያክ ማቻር ተኒና ባለቤታቸው የመከላከያ ሚኒስትሯ አንጀሊና ቲኒ ከሁለት ሳምንታት በፊት ለኮሮናቫይረስ መጋለጣቸው መረጋገጡ ይታወሳል፤ የደቡብ ሱዳን መንግሥት ቃል አቀባይ ማይክል ማኩዊ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ እርሳቸውን ጨምሮ አስራ አምስቱም የሀገሪቱ የፀረ ኮቪድ-19 ግብረ ኃይል አባላት በሙሉ በምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ማስታወቃቸው አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG