በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንቱ ልብሳቸው ላይ መሽናታቸውን ከሚያሳይ ቪዲዮ ጋር በተገናኘ 6 ጋዜጠኞች ታሠሩ


የደቡብ ሱዳን ካርታ
የደቡብ ሱዳን ካርታ

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በአንድ ኦፊሴላዊ ሥነ-ሥር ዓት ላይ ልብሳቸው ላይ መሽናታቸውን የሚያሳይ ቪዲዮ ከመሠራጨቱ ጋር በተገናኘ ስድስት ጋዜጠኞች መታሠራቸውን ሮይተርስ የአገሪቱን ብሔራዊ ጋዜጠኞች ኅብረት ጠቅሶ ዘግቧል።

ባልፈው ወር በተካሄደ አንድ የመንገድ ሥራ ሥምምነት ሥነ-ሥርዓት ላይ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘመር ቆመው የሚታዩት የ71 ዓመቱ ሳልቫ ኪር ግራጫ ሱሪያቸው ረጥቡ ተስተውሏል።

ቪዲዮው በቴሌቪዥን ባይሰራጭም፣ በኋላ ግን በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ተዘዋውሯል።

ለደቡብ ሱዳን ማሠራጫ ኮርፖሬሽን የሚሰሩት ጋዜጠኞች ባለፈው ማክሰኞ መታሠራቸውን የጋዜጠኛ ኅብረቱ ፕሬዚዳንት ፓትሪክ ኦየት ተናግረዋል።

ጋዜጠኞቹ ፕሬዚዳንቱ ላያቸው ላይ ሲሸኑ የሚያሳየው ቪዲዮ ምንጭ ከየት እንደሆነ ስለሚያውቁ ተጠርጥረው መያዛቸውን የኅብረቱ ፕሬዚዳንት ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ሳልቫ ኪር ደቡብ ሱዳን ነፃነቷን ካወጀችበት ከእአአ 2011 ጀምሮ በፕሬዚዳንትነት ቆይተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ጤነኛ አይደሉም የሚለውንና በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሠራጨውን ወሬ የደቡብ ሱዳን ባለሥልጣናት ያስተባብላሉ።

አገሪቱ ላለፉት አስርት ዓመታት በግጭት ስትተራመሥ ቆይታለች። በሕጉ መሠረት ባለሥልጣናት ተጠርጣሪዎችን ዳኛ ፊት እስኪቀርቡ መያዝ የሚችሉት እስከ 24 ሰዓት ብቻ ነው፡፡

“ሁኔታው የአገሪቱ ባለሥልጣናትን በተመለከተ የሚወጡ ዘገባዎች አዎንታዊ ካልሆኑ የጸጥታ ባለሥልጣናት በዘፈቀደ እንደሚያሥሩ ማሳያ ነው” ሲሉ የጋዜጠኞች መብት ተከራልካሪ ቡድኑ ሲፒጄ የሳሃራ በታች አገሮች ተወካይ ሙቶኪ ሙሞ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG