በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን ተቋርጦ የቆየው የነዳጅ ዘይት ምርት መቀጠሉ ተገለፀ

FILE - South Sudan's Oil minister Ezekiel Lul Gatkuoth (R) and Sudan's oil minister, Azhari Abdel Qader arrive for a ceremony marking the restarting of crude oil pumping at the Unity oil fields in South Sudan, Jan. 21, 2019.

በደቡብ ሱዳን የቀድሞዋ ዩኒቲ ስቴት በመንግሥት ወታደሮችና በአማፅያን መካከል ሲካሄድ በቆየው ውጊያ ምክንያት ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የነዳጅ ዘይት ምርት ቀጥሏል።

በደቡብ ሱዳን የቀድሞዋ ዩኒቲ ስቴት በመንግሥት ወታደሮችና በአማፅያን መካከል ሲካሄድ በቆየው ውጊያ ምክንያት ለ5 ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የነዳጅ ዘይት ምርት ቀጥሏል።

የደቡብ ሱዳን የነዳጅ ዘይት ሚኒስቴር አካል የሆነው የፔትሮለም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዎው ዳንኤል ቹአንግ - እንደተናገሩት ሠራተኞች በግጭቶች ወቅት ጉዳት የደረሰባቸውን መሣሪያዎች መልሰው ከጠገኑ በኋላ - በአንዳንድ የዩኒቲ ስቴት አካባቢ እአአ 2018 መጨረሻ ላይ እንደገና ማምረት ተጀምሯል።

በዩኒቲ ስቴት በቀን 20ሺህ በርሜል ነዳጅ ዘይት ብቻ እንዲመረት መወሰኑንም ባለሥልጣኑ ጨምረው አስረድተዋል።

ደቡብ ሱዳን እአአ በ2013 ነጻነቷን ካገኘች ጀምሮ አብዛኛውን የውጭ ምንዛሪ የምታገኘው ወደ ውጭ ሃገር ከምትልከው የነዳጅ ዘይት ሽያጭ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም የርስ በርስ ጦርነቱእአአ በ2013መጨረሻ ላይ በመፈንዳቱ የነዳጅ ምርቱ ሙሉ በሙሉ ተቋርጦ መቆየቱ ይታወቃል።

በቅርቡ አዲስ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ጁባ ላይ ከተከፈተ በኋላ የነዳጅ ምርቱን በቀን ወደ 60ሺህ በርሜል ማሳደግ ይቻላል ሲሉ የፔትሮለም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዎው ዳንኤል ቹአንግ ጨምረው አስረድተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG